ይህ ክፍል ህብረተሰቡ የተፋሰስ ሀብቱን በዘላቂነት እንዲጠብቅ፣ እንዲያለማ እና እንዲጠቀም የወጣውን የህግ ማዕቀፉ ያደረገውን ድጋፍ በተመለከተ የአማራ ክልልን ተሞክሮ ያቀርባል። በክልሉ የተፋሰስ ተጠቃሚዎች ማህበራትን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ(204/2005) የመጀመርያው በህብረተሰቡ የለሙና የሚለሙ ተፋሰሶችን አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓት ለማስያዝ ኃላፊነትን ለአካባቢው ማህበረሰብ የሰጠ አንደነበር እንደ ልምድ እንዲታይ የቀረበ ነው፡፡